አፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታል C-arm በማስገባት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል

ታካሚዎቹን ፍላጎት ለማሟላት ዘመናዊ የሕክምና መሳሪያዎችን በቀዳሚነት በማስመጣት አገልግሎት በመስጠት ፈር ቀዳጅ የሆነው #አፊላስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የአጥንት ሕክምናን በብዙ ዘርፍ የሚያዘምን እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ (C-ARM) ለከተማችን በብቸኝነት አስመጥቶ #አገልግሎት_እየሰጠ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። 

በመሳሪያው በመታገዝ:
* ውስብስብ ስብራቶች ሕክምና 
* የዳሌና ዳሌ ገንዳ ስብራቶች ሕክምና 
* የመገጣጠሚያ ከባቢ ስብራቶች ሕክምና 
* ቆዳ ሳይከፈት የልጆች አጥንት ስብራት ሕክምና 
* የልጆች አጥንት እድገት ማስተካከል
* የተጣመመ እጅ/እግር (አቋቋም) ማስተካከል ህክምና
* በተፈጥሮ ወይንም በአደጋ የወለቀ መገጣጠሚያ ሕክምና 
* የአከርካሪ አጥንትና ሕብረ-ሰረሰር ህክምናና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን #በሰብ_ስፔሻሊስት ሃኪሞች እየሰጠን መሆኑን እየገለፅን ለነዚህ ሕክምናዎች በሪፈር ምክንያት ከሚደርስ የታካሚዎች እንግልትና ወጭ በመቀነስ በኩል የበኩላችን ማህበራዊ ግዴታ መወጣት በመቻላችን ታላቅ ኩራት የተሰማን መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን:: 

አድራሻ፣ ባህር ዳር

የአማራ ህብረተሰብ ጤና ምርምር ማዕከል ፊት ለፊት::

ለመረጃ ስልክ ቁጥሮች:

+251930316768

+251583204167 ይደውሉ።

የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን አባል በመሆን የጤና ምክረ-ሃሳቦችን ይጋሩ፤

– ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Afilas-General-Hospital-አፊላስ-ጠቅላላ-ሆስፒታል-112500166795773/

– ቴሌግራም: https://t.me/Afilas_PRelation

– ኢንስታግራም: https://instagram.com/afilas_general_hospital_bdr?igshid=ZDdkNTZiNTM=