- March 21, 2022
- Editor
- Comment: 0
- Uncategorized
75 በላይ በሆኑ ሐኪሞች
እና የጤና ባለሞያዎች የተቋቋመው እና ላለፉት ሁለት ዓመታት የተለያዩ
የህክምና አገልግሎቶችን አገር ወዳድ፣ ለሙያቸው ክብር ባላቸው እና መልካም የሙያ ሥነ ምግባር በተላበሱ ሐኪሞች ሲሰጥ የነበረው
አፊላስ የፋርማሲውቲካልስ ማምረቻ እና የህክምና አገልግሎት አክሲዮን ማኅበር
አሁን ደግሞ ጥራቱን እንደጠበቀ ልዩ የሚያደርጉትን የተለዩ አገልግሎቶችን አካቶ በከተማችን ብሎም በክልላችን አዳዲስ
አማራጮችን ይዞ በአዲስ መልክ ብቅ አለ፡፡
ማናኪ የታካሚዎችን እንግልት ለመቀነስ
በሚያስችል መልኩ የሚሰራ ሲሆን በጣም ወጪ ቆጣቢ፣ የላቀ ቴክኖሎጂን መሰረት ባደረገ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ አገልግሎቱን
ከመስጠቱም ባሻገር ለታካማች የህክምና ቪዛ በቀላሉ ለማግኝት የሚያስች አሰራርን ይከተላል፡፡ በዋነኛነት ታካሚዎች ከቤታችው ወጥተው
ቤታቸው እንኪመለሱ ድረስ የጉዞ መርጃን በመስጠት፣ ከአየር ማረፊያ በመቀበል እና ወደ ሆሰፒታል በማድረስ፣ የማረፊያ ቦታ በማዘጋጀት፣
ተስማሚ ምግብና የጸሎት ቦታ እንዲያገኙ በማመቻቸት እና መሰል ተግባራትን በመፈጸም ታካሚዎችን በቅርብ በመከታተል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ
የሚሰራ ድርጅት ነው፡፡
በዛሬው እለት አፊላስ ጠቅላላ
ሄስፒታል እና ማናኪ ህልዝ ኬር ለባህር ዳር ከተማ እና ለአካባቢ ነዋሪች በቅርበት ለማገልገል የሚስችለንን ስምምነት አድርገናል፡፡